Search    
Friday, September 03, 2010 ..:: News and Articles » Reading Articles ::.. Register   Login
 Amharic Fonts Minimize

If you can't read the following Amharic text please download the Amharic UNICODE fonts and copy them in your windows/fonts directory manually from the following link.

 እንደ ዳዊት ባርኮታችንን በመቍጠር እግዚአብሐርን ለማመስገንና ለማምለክ 

Download from here.

Find the download button at Right-Bottom


Syndicate    Print    
 Article Categories Minimize

 Print    
 Reading Articles Minimize

Current Articles | Categories | Search | Syndication

Thursday, September 18, 2008
ሦሰት ጉልቻ
By mnegusse @ 6:31 PM :: 1534 Views :: 2 Comments :: :: Family Matters
 

ሦሰት ጉልቻ

 

የተለያዩ ባሕሎችና ቋንቋዎች ጋብቻን ለመግለጽ የሚጠቀሙባቸው የየራሳቸው የሆኑ ዘይቤዎች አሏቸው። “ሦስት ጉልቻ” ደግሞ አበው ከተመክሮ በቀሰሙት ጋብቻን  ለመግለጽ የተጠቀሙት የራሳችን ዘይቤ ነው። ጋብቻን በዚህ አባባል ለመግለጽ ሲሞከር ትዳር ከሁለት ሰዎች ጥምረት ባሻገር ሊስተዋል የሚገባው እውነታ እንዳለው ይታያል። አባባሉ አባቶቻችን በተመክሮ ጋብቻ ከታጋቢዎቹ ሁለትነት የዘለለ ገጽታ እንዳለው መረዳታቸውን የሚመሰክር ነው።

 

ባደግንበት ባሕል ክልል ተወስነን ለምንኖረውም ሆነ የባህሉን ድንበርን ክልል አለፈን፣ በረሃውን አቋርጠን፣ ባሕሩን ተሻግረን ለምንኖረው ሁሉ ይህን አባባል በተመለከተ ለማሰተላለፍ የምንፈልገው መልእክት አለን። አማኞች በትዳራቸው ጸንተው አምላካቸውን የሚያሰከብር የትዳር ኑሮ መምራት እንዲችሉ ማስተማር፣ መምከርና ማበረታታት አንዱ የቤተ ከርስቲያን ተልዕኮ ነው የሦሰት ጉልቻ ዋና አሳብም ባልና ሚስት መልካም ትዳር ለመምራት እግዚአብሔርን በሦሰተኛነት ወደ ኑሮአቸው ሊጋብዙት እንደሚያሰፈልጋቸው መጠቆም  ነው።

 

ከሁሉ በፊትትዳር ከየት መጣ? የትዳርስ ፈጣሪ ማን ነው?” የሚሉትን ጥያቄዎች ማንሣትና መልሶችን መስጠት እጅግ አስፈላጊ ነው። በዚህ ዓለም ያሉ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ሁሉ ሠሪ እንዳላቸው ሁሉ፡ በወንድና በሴት መካከል ያለው ትዳርም ፈጣሪ ወይም ሠሪ አለው። እርሱም ሰማይን፡ ምድርንና ባሕርን በውስጣቸውም የሚኖሩትን ሁሉ የፈጠረ አምላካችን እግዚአብሔር ነው።

 

ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር” በማለት ከትዳር በፊት እግዚአብሔር ሰውን በራሱ መልክና ምሳሌ እንደ ፈጠረ የእግዚአብሔር ቃል ያስተምረናል። ዘፍጥረት 1፡26-27 “ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው” ይላል። ቀጥሎም “ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም፤ የሚመቸውን ወይም እንደ እርሱ ያለ ረዳት እንፍጠርለት” (ዘፍጥረት 2፡18፣21) በማለት ጌታ እግዚአብሔር ጋብቻን ለሰው ብቸኝነት መፍትሔ አድርጎ እንደፈጠረ ከቅዱስ ቃሉ እንማራለን።

 

      የእግዚአብሔር አሳብ ይህ ሆኖ ሳለ የሰው ልጅ በአሁኑ ሰዓት የሚገኘው ግን ባለትዳሮች በበርካታ ችግሮች ውስጥ በሚያልፉበት ዘመን ነው። ከዚህም የተነሣ ትዳርን ማፍረስና ቤተሰብን መበተን ለብዙዎች የማያዳግት ምርጫ ሆኗል። በአንድ ወላጅ ብቻ የሚያድጉ ሕፃናት የዚህ ችግር ሰለባ ሆነዋል።

 

ጋብቻ ጣዕም ያለው እንዲሆን  ባልና ሚሰት ከሁሉ በተቀዳሚ እግዚአብሔርን በሦስተኛነት ወደ ትዳራቸው ማስገባታቸው አማራጭ ሳይሆን አሰፈላጊ ነው። የትዳር ፈጣሪ የሆነው እግዚአብሔር ቅዱሰ ትዳርን የሚመራበት ግሩም የሆነ የመመሪያ ቃል አለውና! ያለዚያ ትዳር ፍሬ የሌለው የአፈርና የአጥንት ብረት ብቻ ይሆንና ሦሰት ጉልቻ ትርጉም የለሸ ኑሮ ይሆናል።  ከኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን የጋብቻ አገልግሎት።

Rating
Comments
By getachew @ Friday, October 03, 2008 9:25 AM
Yes, everybody agree that marriage is a blessing; it’s a gift of God. I’m a divorcee. I’m happier now that I was with my ex-wife. The only pleasure I yielded from that marriage is my kids. Apart from this the eight years marriage life is like sleeping on a hot frying pan. SOST GULICHA might be good; however, sometimes it’s a remedy to split-up and live alone; even divorce can save kids from being orphans (hope you understand me what I wanted to say-we’re in the era of AIDS). What is your thought on this point? Let’s discuss on it.

By Torrent Search Engine @ Thursday, December 24, 2009 5:31 AM
I agree with the idea that when two people cease to love each other, it seems to be much better for both and for their children, if they have any, to get divorced. That is my personal point of view, of course, but there exists a good deal of examples, which prove that in a proper way.

Click here to post a comment

 Print    
 Advertize here Minimize

Syndicate    Print    
© 1999 - 2007 Ethiopian Evangelical Church in Toronto    Terms Of Use   Privacy Statement