“ሁሉም ወደ ንስሐ እንዲደርሱ እንጂ ማንም እንዳይጠፋ!”
2ኛ ጴጥ.፡ 3 ፥ 9
ምንባብ፦ 2ኛ ጴጥ.፡ 3 ፥ 8 - 18
1. “ለአንዳንዶች እንደሚመስላቸዉ”ጌታ ስለ ተስፋ ቃሉ አይዘገይም!
ይህ ሁለት አይነት ጊዜን ያሳያል
ሀ. የሰዉ ጊዜ
ለ. የእግዚአብሔር ጊዜ
እግዚአብሔር ሕዝቡን ለመታደግ ያዘጋጀዉ ቀነ ቀጠሮ አለዉ!
- በእርግጥ ዓዉደ ንባቡ (ኮንቴክስቱ) የሚናገረዉ ስለ ጌታ ዳግም መምጣት ቢሆንም
- ለሰዉ ግን ሁልጊዜ ጌታ የዘገየ ይመስላል
ለሰዎች መዘግየት የሚመስላቸዉ በጌታ ዘንድ ግን ትዕግስት ነዉ፥ ያዉም ስለ እኛ መታገሡ
ሀ. ዓለም ከመፈጠሩ በፊት ለመንግስቱ የታጩት ወንጌልን ሰምተዉ እንዲድኑ
ለ. የዳኑት ነገር ግን እምነታቸዉ የዛለባቸዉ ባልሆነ መንገድ የተጠላለፉ እንዲመለሱ
2. የጌታ ቀን
- ለቅዱሳን የሚያስደስት ቀን፥ ለዓለም ግን የሚያስፈራ ቀን
- “የጌታ ቀን እንደ ሌባ ሆኖ ይመጣል”
3. ዓለም አቀፍ ለዉጦች (ግሎባል) ምልክቶች
ከጌታ ዳግም ምጽአት ጋር የተያያዙ ሰባት ዋና ዋና ትንቢታዊ ምልክቶች እየተፈጸሙ ናቸዉ!
ሀ. እስከ አሁን የተፈጸሙ
1. እስራኤል ከ2000 የስደት ዘመን በኋላ ግንቦት 15 ቀን 1948 ወደ ሃገራቸዉ ተመልሰዉ መንግስት አቋቋሙ (አሞጽ 9 ፥ 14 – 15 ፣ ሕዝ. 38 ፥ 8)
2. ኢየሩሳሌም በአይሁድ ቁጥጥር ስር ትሆናለች (ሉቃ. 21 ፥ 24) “የአህዛብ ዘመን እስኪፈጸም ድረስ ኢየሩሳሌም በአህዛብ የተረገጠች ትሆናለች”
ለ. በመፈጸም ላይ በሂደት ላይ ያሉ
3. በራሺያ አስተባባሪነት ዓለም- አቀፍ የእስልምና ግንባር እስራኤልን ይወጋሉ (ሕዝ. 38)
4. የቀድሞዉ የሮም መንግስት እንደ አንድ ትልቅ መንግስት ያቆጠቁጣል - የአዉሮፓ ሕብረት (ራዕ. 17 ፥ 9 – 10)
5. ዓለም አንድ ሃይማኖት ይኖራታል (ራዕ. 13 ፥ 8)
6. ዓለም አንድ መንግሥት ትሆናለች (ራዕ. 13 ፥ 3)
7. ባቢሎን የዓለም ዋና ከተማ ሆና ብቅ ትላለች (ራዕ. 18 ፥ 2 – 3)
ማቴ. 24
- ግሎባል ረሃብ
- ግሎባል ቸነፈር
- ግሎባል የምድር መናወጥ
ማር. 13 ፥ 8
- በልዩ ልዩ ስፍራ የምድር መናወጥ ይሆናል
- ራብ ይሆናል
- እነዚህ የምጥ ጣር መጀመሪያ ናቸዉ
ሐዋርያዉ ጳዉሎስ “የሚያስጨንቅ ዘመን” ይለዋል፥ አጠቃላይ ሰዎች፦ (2ጢሞ. 3)
- ራሳቸዉን፥ ገንዘብን የሚወዱ ይሆናሉ
- ትምክህተኞች
- ትዕቢተኞች
- ተሳዳቢዎች
- ለወላጆቻቸዉ የማይታዘዙ
- የማያመሰግኑ
- ቅድስና የሌላቸዉ
- ፍቅር የሌላቸዉ
- ዕርቅን የማይሰሙ
- ሓሜተኞች
- ራሳቸዉን የማይገዙ
- ጨካኞች
- መልካም የሆነዉን የማይወዱ (ከቴሌቪዥን ጀምሮ)
- ከዳተኞች
- ችኩሎች
- በትዕቢት የተነፉ
- ከእግዚአብሔር ይልቅ ተድላን የሚወዱ
- የአምልኮት መልክ አላቸዉ፥ ኃይሉን ክደዋል
ቤበተ ክርስቲያን ዉስጥ ደግሞ (2ጴጥ ፥ 2)
4. በድንገት ይመጣባቸዋል (1 ተሰሎ. 5፥ 3)
5. በሰዉ ሁሉ ፍርሃት፥ ስጋትና ጭንቀት ይበዛል
6. መንፈሳዊ መሳት - ኢየሱስን ሳይሆን ምልክትና ተአምራት ፍለጋ መኳተን
የእዉነተኛ ምልክትና ተአምራት ምልክቶች፦
1. ቃሉን የሚያጸና
2. እየሱስ ክርስቶስን ከፍ ከፍ ያድርጋል
3. ሰዎች በብዛት ወደ ጌታ እንዲመጡ ይረዳል
4. አማኞችም በንስሐ ሕይወት እንዲዘጋጁ ያደርጋል
5. የቃሉን ጥማት፥ የጸሎትን ጥማት ይለቃል
6. ሰዎች ለቅድስና ይተጋሉ፥ ግልጽ የሆነ የሕይወት ለዉጥ ይታያል
7. የሳቱ ይመለሳሉ
8. የወደቁ ይነሳሉ
7. ዝግጅት
“ምጥ እርጉዝን እንደሚይዛት ጥፋት በድንገት ይመጣባቸዋል” (1ተሰ. 5፥ 3)
- በመንፈስ ማስተዋል “ቀኑ እንደ ሌባ ይደርስባችሁ ዘንድ በጨለማ አይደላችሁም፥ ሁላችሁ የብርሃን ልጆች፥ የቀንም ልጆች ናችሁና” (1ተሰ. 5፥4)
የእግዚአብሔርን ቀን መምጣት እየጠበቃችሁና እያስቸኮላችሁ
እምናስችኩለዉ እንዴት ነዉ?
o እንንቃ
o በመጠን እንኑር (Self Control)
- ያለ ነዉርና ያለ ነቀፋ ሆናችሁ በሰላም በእርሱ እንድትገኙ ትጉ
- Without spot and blameless and perfect
- በዓመጸኞች ስሕተት ተስባችሁ ከራሳችሁ ጽናት እንዳትወድቁ ተጠንቀቁ
- ነገር ግን በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና እዉቀት እደጉ
o መቀደስ
o መጸለይ
o መመስከር